ቅጽሐፍ ቤት / House of commentary

ይህ ገጽ የቅዱሳን መፅሐፍትን ትርጓሜ ያስተምራል!

ንባብ ቤት | ዜማ ቤት | ቅኔ ቤት| ቁጥር ቤት

መፅሐፍ ቤት

በመፅሐፍ ቤትም ከዘፍጥረት ጀምረን እግዚያብሔር እንደፈቀደ በተከታታይ አቅርበናል ፣ እናቀርባለን:: ይህንን ከፍል ቀደም ብለን እንደመጀመራችን መጠን እግዚአብሔር አከናውኖልን ሃዲሳትን ብሉያተን የቻልነውን ያክል ያካተትን ሲሆን እግዚአብሔር ቢፈቅደ ደግሞ የቀሩትን ለመጨመርና ሊቃውንትና መፅሐፈ መነኮሳትንም ለመዝለቅ እናስባለን :: ምዕመናን መምህራነ ወንጌል ተጠቅመውበት ተምረው አስተምረው ንባብን ብቻ ሳይሆን ምስጢርን(ትርጉምን) ጠንቅቀው:በዚህም ከኃጢያት ርቀው ጽድቅን አብዝተው ሰላሳ ሥልሳ እና መቶ ፍሬን አፍርተው ለእነርሱም ለእኛም ጥቅመ ነፍስን እናስገኝለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን:: ለዚህም እዚህ ደርሳችሁ ፋይሎችን ካገኝችሁ በኋላ በመጀመሪያም እንደማንኛውም መረጃ ከመያዝ ይልቅ/በተጨማሪ አድምጣችሁ እንድትማሩ ከዚያም ለሌሎች ወገኖቻችን የተማራችሁት እንድታካፍሉ እንመኛለን:: እንዲህ ከሆነ ሁላችንም ተጋግዘን(ተያይዘን) ተስፋ የምናደርጋትን መንግስተሰማያትን መውረስ ይቻለናልና::


ቸር አምላክ ይግለጥልን!! በጸሎታችሁ አስቡን!

መፅሓፍ ቤት

ብሉይ ኪዳን አንድምታ

አዲስ ኪዳን አንድምታ

ውዳሴ/ቅዳሴ ማርያም አንድምታ

ቅዳሴ አንድምታ

የሊቃውንት አንድምታ

ማር ይስሐቅ

አረጋዊ መንፈሳዊ

ፊልክስዩስ

ግእዝ በግእዝ ትርጓሜ