ይህንን መፅሐፍ ብላ / eathebook

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአብነት ትምህርት መርጃ የድምጽ መዛግብት ቋት!


ንባብ ቤት | ቅኔ ቤት |ዜማ ቤት | መፅሓፍ ቤት | ቁጥር ቤት

መግቢያ

ይህ ድረገጽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የግዕዝ ንባብ:የዜማና የመፅሐፍ ትርጓሜን ለመማሪያ የሚያግዙ የድምጽ መዛግብትን በነጻ ያቀርባል:: በዚህ ዙር በከፈትናቸው በነዚህ ሦስት ቤቶች(ገጾች) ምስክር ባላቸው መምህራን በቆሎ ት/ቤት የሚሄድበት መንገድ ተከትሎ ለማጥናት(ለመቀጸል)በሚያችል ሁኔታ የድምጽ መዛግብቱን ከፋፍለን አቅርበናል:: የአብነት ትምህርት መርጃ የድምጽ መዛግብት ቋት ነው ማለታችንም በተቻለ መጠን የአብነቱን መንገድ ተከትለን የድምጽ መዛግብቱን ለማደራጀት በመጣራችን ነው:: ያላችሁን ሃሳብ በማኅበራዊ ገጾቻችን ወይም በኢሜላችን ብታካፍሉን እግዚአብሔር እንደረዳን መጠን ማሻሻያ ለማድረግ እንደምንጥር ቃል እንገባለን::

ንባብ ቤት

በንባብ ቤት በሦስቱም የንባብ ስልቶች ማለትም ግዕዝ: ውርድ ና ቁም ንባብ መልዕክተ ዮሐንስ ና ወንጌለ ዮሐንስ የቀረቡ ሲሆን የቀሩትን ማተትም የዘውትር ጸሎት ፣ ውዳሴ ማርያም፣ አንቀጸ ብርሃን፣ ይወድስዋ መላእክት፣ መልክዐ ማርያም፣ መልክዐ ኢየሱስ፣ መዘሙረ ዳዊት ወ ጸሎተ ነብያትን በቁም ንባብ አቅርበናል:: በእናንተ ጸሎትና እንደእግዚአብሔር ፈቃድ በዚህ ክፍል በተከታታይም የተለያዩ መፅሐፍትን ንባባ ለማቅረብ እናስባለን::

ቅኔ ቤት

ይህ ድረገጽ ለግዕዝ ቋንቋን ና ቅኔን ለመማር የሚጠቅሙ የድምጽ መዛግብትን(audio books) ያቀርባል:: አብዛኛው ይዘት መሠረታዊውን የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዳይለቅ በማሰብ ሰዋስወ ግእዝ ከሚባለው መፅሐፍ መየተወሰደ ነው፡፡ ይህም መፅሐፍ እንደሚታወቀው በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ታርሞና ተስተካክሎ በትንሣኤ ማተሚያ ቤት የታተመ ነው፡፡

ዜማ ቤት

በዜማ ቤትም መሠረታዊ ያሬዳዊ ዜማን ለመማሪያነት የሚጠቅሙ የድምጽ መዛግብትን ለማጥናት በሚመች መጠን ተከፋፍሎ ቀርቧል:: በተቻለ መጠን በዜማ ቤት በሚጠናበት ቅደምተከለልም ለማቅረብ እንሞክራለን: በተለይም የሥረይ ምልክቶችን እንደመሰረታዊ የጥናት ዘዴ በመጠቀምን አስፋፍተን ለመቀጠል ተስፋ እናደርጋለን:: እስክሁን ድረስም ከሰኞ እስክ ቅዳሜ ( አራራይ) የእሁድ ስረይ ምልክቶች(እዝል)፣ ውዳሴማርያም፣የቅዳሴ ቃል ትምህርት፣ መስተጋብዕ ፣ አርባዕት ፣ አርያም ፣ ሰልስት ፣ የዐቢይ ጾም ዜማዎች ፣ የመወድስ ምዕራፍ ፣ የዋዜማ ምዕራፍ ፣ የሥብሃተ ነግህ ምዕራፍ ፣ የምዕራፍ መስተብቍዕ:ሊጦን: ዘይነግስ ኪዳን ፣ የዘወረደ ጾመ ድጓ ፣ የቅድስት ጾመ ድጓ ፣ የምኩራብ ጾመ ድጓ ፣ የመጻጉ ጾመ ድጓ ፣ ተዘጋጅቶ ቀርቧል:: በተከታታይአም በዚሁ ቅደም ተከተል የምንቀጥል ይሆናል::

መፅሐፍ ቤት

በመፅሐፍ ቤትም ከዘፍጥረት ጀምረን እግዚያብሔር እንደፈቀደ በተከታታይ አቅርበናል ፣ እናቀርባለን:: ይህንን ከፍል ቀደም ብለን እንደመጀመራችን መጠን እግዚአብሔር አከናውኖልን ሃዲሳትን ብሉያተን የቻልነውን ያክል ያካተትን ሲሆን እግዚአብሔር ቢፈቅደ ደግሞ የቀሩትን ለመጨመርና ሊቃውንትና መፅሐፈ መነኮሳትንም ለመዝለቅ እናስባለን :: ምዕመናን መምህራነ ወንጌል ተጠቅመውበት ተምረው አስተምረው ንባብን ብቻ ሳይሆን ምስጢርን(ትርጉምን) ጠንቅቀው:በዚህም ከኃጢያት ርቀው ጽድቅን አብዝተው ሰላሳ ሥልሳ እና መቶ ፍሬን አፍርተው ለእነርሱም ለእኛም ጥቅመ ነፍስን እናስገኝለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን:: ለዚህም እዚህ ደርሳችሁ ፋይሎችን ካገኝችሁ በኋላ በመጀመሪያም እንደማንኛውም መረጃ ከመያዝ ይልቅ/በተጨማሪ አድምጣችሁ እንድትማሩ ከዚያም ለሌሎች ወገኖቻችን የተማራችሁት እንድታካፍሉ እንመኛለን:: እንዲህ ከሆነ ሁላችንም ተጋግዘን(ተያይዘን) ተስፋ የምናደርጋትን መንግስተሰማያትን መውረስ ይቻለናልና::

የቁጥር ቤት

ይህ ድረገጽ የቤተክርስቲያን ቀን ቁጥርና ሌሎችንም የቁጥር ትምህርቶችን ለማጥናት የሚረዱ የድምጽ መዛግብትን(audio books) ያቀርባል:: ይዘቱ መሠረታዊውን የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዳይለቅ በማሰብ አቡሻኸር እና ከሌሎችም የታተሙ መፅሐፍት የተወሰደ ነው፡፡

ሃሳባችሁን አስተያለታችሁን ፍላጎታችሁን በማህበረሰብ ገጾቻችን በኩል ብታደርሱን እንወዳለን::


ቸር አምላክ ይግለጥልን!!

ቅኔ ቤት

ንባብ ቤት

መዘሙረ ዳዊት ወ ጸሎተ ነብያት

መልክዐ መልክ

መዘሙረ ዳዊት ውርድ ንባብ

የሐዲስ ኪዳን ግዕዝ ንባብ

የብሉይ ኪዳን ግዕዝ ንባብ

ከ81 መጽሐፍ ቅዱስ 2ኛ የቀኖና መጽሐፍት የአማርኝ ንባብ

ሃይማኖተ አበው፤ ስንክሳር፤ ፍትሃ ነገሥት፤መጽሐፈ ምሥጢ፤ በግእዝ ንባብ

ግብረ ህማማት

 

ዜማ ቤት

የዐቢይ ጾም ዜማዎች

የመወድስ ምዕራፍ

የዋዜማ ምዕራፍ

የሥብሃተ ነግህ ምዕራፍ

የምዕራፍ መስተብቍዕ:ሊጦን: ዘይነግስ ኪዳን

የዘወረደ ጾመ ድጓ

የቅድስት ጾመ ድጓ

የምኩራብ ጾመ ድጓ

የመጻጉ ጾመ ድጓ

የደብረዘይት ጾመ ድጓ

የገብርሄር ጾመ ድጓ

የኒቆዲሞስ ጾመ ድጓ

የሆሣዕና ጾመ ድጓ

ድጓ

የእለት መዝሙራት

የቅዳሴ ቃል ትምህርት

ሥርዓተ ቅዳሴ

ኪዳንና ሰዓታት

 

መፅሓፍ ቤት

ብሉይ ኪዳን አንድምታ

አዲስ ኪዳን አንድምታ

ውዳሴ/ቅዳሴ ማርያም አንድምታ

ቅዳሴ አንድምታ

የሊቃውንት አንድምታ

ማር ይስሐቅ

አረጋዊ መንፈሳዊ

ፊልክስዩስ

ግእዝ በግእዝ ትርጓሜ

 

ቁጥር ቤት